Vehicle and Machinery Foreclosure
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ማስተካከያ አድርጎበታል
Description
የጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ንብ/019/2019
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሪፖርተር ጋዜጣ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ ማስታወቂያ ያወጣ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ከታች በተጠቀሰው መሰረት የተቀየረ መሆኑን እንገልጻለን።
1. ጨረታው በባንኩ የግዢ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው የግልጽ ጨረታ ሂደት መስረት ይከናወናል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ብር አምስት መቶ/ በንብ ባንክ አካውንት ቁጥር ETB1764600010001 በቅድሚያ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ሰነዱን የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሱትን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎቹን ባሉበት ሁኔታ ለመመልከት የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2:00 - 6፡00 ሰዓት እና ከ 7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ሪቼ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ የወደፊት ግንባታ ቅጥር ግቢ እና አራት ኪሎ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቶች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከታች በተራ ቁጥር 7 ስር በተጠቀሰው አድራሻ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው:: ዘግይቶ የደረሰ መወዳደሪያ ተቀባይነት አይኖረውም።
5. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ከዋናው የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ አለባቸው።
6. ከላይ የተዘረዘሩት የሚሸጡ ከላይ በሰንጠረዥ ያገለገሉ ዕቃዎች ላይ የተ.እ.ታ. ይታሰባል።
7. ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 9፡15 ሰዓት ሰንጋ ተራ በሚገኘው ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 26ኛ ፎቅ ግዢ ዋና ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ስልክ ቁጥር 0115-50-44-52 /0116 29 62 46 / 0115 51 26 50
ፋክስ 0115622448
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tenders.qelal.et/tender-6a8c488e0a538a10a5000001/
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-10-20 15:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nib International Bank S.C.
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T12:47:25.000Z
- Source: Qelal Tenders