Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase

ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች እና ሞተር ብስክሌቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
KALITI METAL PRODUCTS FACTORY
Document No. OF/kMPF/254 (Pr No 008)
Tender No. 01/2019

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ቀጥሎ የተመለከቱትን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች እና ሞተር ብስክሌቶች ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. አነስተኛ አውቶሞቢል በኤሌክትሪክ የሚሰራ ብዛት 3
  2. መለስተኛ የሰራተኛ ሰርቪስ አውቶብስ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ብዛት 1
  3. በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሞተር ብስክሌቶችብዛት 2

ስለሆነም ፡

1. የታደሠ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ማስረጃ በሚመለከተው መ/ቤት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ወይም በመንግስት የአቅራቢነት ዝርዝር ኤሌክትሮኒክ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ከካፍደም ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

3. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሠነዶቻችውን ለይተው በማሸግ በፖስታ በማድረግ ከመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:።

6. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 434 0110 Ext 306/305
ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-02 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsehay Industry S.C.
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T13:09:26.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders