Stationery

ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር- JM 03 /2019

ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በዝርዝር የተቀመጡትን ሎት1 የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት 2 የጽዳት መገልገያ እቃዎች ሎት 3 የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች፤ ሎት 4 ብረታብረቶች እና የብየዳ እቃዎች /Metals and welding materials/፤ ሎት 5 የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና የጥንቃቄ ዕቃዎች ሎት 6 የኤሌክትሪክ እቃዎች፤ ሎት 7 የተለያዩ ቀለሞች፤ ሎት 8 የማሽን መሣሪያዎች (machine shop tools) ፤ ሎት 9 በፋብሪካ ውስጥ የመለኪያ መሣሪያዎች/Hand tools / ሎት 10 ቅባት ና ነዳጅ (lubricant and Gas)፤ ሎት 11 የመኪና መለዋወጫና ሰርቪስ /Car spar part materials/ ሎት 12 ደብል ካቢን ፒካፕ መኪና Double cabin pickup car 2025/26 ለሁለተኛ ጊዜ በወጣው ግልጽ ጨረታ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈለጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

የእቃ ዝርዝር

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (ETB)

ሎት 1

የጽሕፈት መሣሪያዎች ( stationery)

4,000

ሎት 2

የጽዳት መገልገያ እቃዎች (sanitary)

4,000

ሎት 3

የቢሮ ቋሚ እቃዎች / office furniture

7,000

ሎት 4

ብረታ ብረቶች እና የብየዳ እቃዎች /Metals and welding materials/

10,000

ሎት 5

የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና የጥንቃቄ እቃዎች ( uniform or safety cloth & safety equipment)

3,000

ሎት 6

የኤሌክትሪክ እቃዎች | Electric Materials

4,000

ሎት 7

ቀለሞች / METALC PAINTS

3,000

ሎት 8

የማሽን መሣሪያዎች /Machine Shop Tool |

20,000

ሎት 9

በፋብሪካ ውስጥ የሚያገለግሉ የእጅ መሣሪያዎች | HAND TOOLS

3,000

ሎት 10

ቅባትና ነዳጅ (lubricant and Gas)

5,000

ሎት 11

የመኪና መለዋወጫና ሰርቪስ /Car spar part materials/

5000

ሎት 12

ደብል ካቢን ፒካፕ መኪና Double cabin pickup car 2025/26

10000

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላሉ።

7. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኮፒ በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለዉ በመለየትና በ2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ቦታ ከተማ አስተዳደር አከባቢ አቡ ሴራ ሁለገብ ሥ/ማህበር ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ጀብዱ ሞተርስ ኢማ ጽ/ ቤት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በዕለቱ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ቦታ ከተማ አስተዳደር አከባቢ አቡ ሴራ ሁለገብ ህ/ሥ/ ማህበር ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ጀብዱ ሞተርስ አማ ጽ/ቤት ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡09 88 85 00 96/ 09 41 07 72 74 Email:- [email protected] 

ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ
  • Bid opening: 2026-10-02 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jebdu Motors S.C.
  • Buyer address: ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ቦታ ሰንሻን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T07:37:33.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders