Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናስና ፕላን መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceAudio Visual, Photography and Filming Service and EquipmentArt
South Ethiopia Regional State
Description
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናስና ፕላን መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ማለትም ሎት1. የጽዳት ዕቃዎች ሎት2. ካሜራ እና መለዋወጫዎች ሎት 3. ሞተር ሳይክል ሎት 4. በአከባቢ ማቴሪያል ሆኖ በዘመናዊ ማሽን የሚሰሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- በዘመኑ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ማቀረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
ከላይ በዝርዝር የተቀመጠዉን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ፤
- ሎት 1. የጽዳት ዕቃዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት 2. ካሜራ እና መለዋወጫዎች ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- ሎት 3. ሞተር ሳይክል ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- ሎት 4. በአከባቢ ማቴሪያል ሆኖ በዘመናዊ ማሽን የሚሰሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ፈርኒቸር ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ ሲፒኦ እና በባንክ ዋሰትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኃላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
- ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፤
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች ጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን በኃላ ለ3 ወር ማለትም ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 131 0108 መደወል ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናስና ፕላን መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-06 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Gedeo Zone Finance and Economic Development Command Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T08:14:39.000Z
- Source: 2merkato