Textile, Garment and Leather

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ- ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቆች)፣ አዳዲስ አልባሳት (ጫማዎች) እና አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) በሐራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሐራጅ ቁጥር 07/2019

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ- ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቆች)፤ አዳዲስ አልባሳት (ጫማዎች) እና አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) በሐራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ ሰነዱን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

የጨረታ አይነት

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታው የታተመበት ቀን

ጨረታው ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

 

ጨረታው የሚጀምር ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

 

ስልክ ቁጥር

 

1

አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቆች)

ሐራጅ

11/01/2019

 

16/01/2019

 

8:00

9:00

0221118429/

0222118925

2

አዳዲስ አልባሳት (ጫማዎች)

ሐራጅ

11/01/2019

16/01/2019

8:00

9:00

0221118429/

0222118925

3

አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች)

ሐራጅ

11/01/2019

16/01/2019

8:00

9:00

0221118429/

0222118925

5. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።

6. በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 1 አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቆች) ብር 3,915,400.00 ፣ ለምድብ 2 አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቆች) ብር 1,985,000.00 ፣ ለምድብ 3 አዳዲስ አልባሳት (ጫማዎች) ብር 282,500.00፣ ለምድብ 4 አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) ብር 1,880,000.00 ፣ ለምድብ 5 አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) ብር 2,410,100.00 በ (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

7. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 እንዲሁም ብዛቱ 556pak አዳዲስ አልባሳት(የሱፍ ጨርቆች) በአዳማ ቆርቆሮ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 05 ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማየት እና መጫረት ይቻላል።

8. በሐራጅ ጨረታ እቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

11. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

NB: በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራጮች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙትን ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግና እቃው በድጋሚ ጨረታ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት

ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-26
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-26 15:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T08:52:23.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders