Vehicle (garage service)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መኪና በዘርፉ በተሰማሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል

Description

የተሽከርካሪ ጥገና ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሎት 1. የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ ንብረት የሆነው ታታ የጭነት መኪና ሎት 2. የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ንብረት የሆነው ሚትስቡሽ መኪና ሎት3. የጌዴኦ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ንብረት የሆነው ሚትስቡሽ መኪና በዘርፉ በተሰማሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  • የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

    • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
    • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 60,000 / ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  • ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፤
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-131-01-08 መደወል ይችላሉ፡፡

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ዲላ/


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Gedeo Zone Finance and Economic Development Command Bureau
  • Bid bond: 60,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T09:09:04.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders