Stationery
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ማዕከላት የሚያገለግሉ የተለያየ ዓይነት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU/DMR/SPG/NCB-001/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ማዕከላት የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዬ ዓይነት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃ ዓይነት |
ሎት |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) |
ጨረታዉ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን |
|
1. |
የተለያዩ አይነት እስቴሽነሪዎች |
ሎት 1 |
3,631 |
42,700(አርባ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ብር) |
26/01/2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
|
2. |
ስካነር |
ሎት 2 |
5 |
4,200(አራት ሺ ሁለት መቶ ብር) |
26/01/2019 ዓ.ም 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
|
3. |
የተሸከርካሪዎች ዘይት እና ግሪስ |
ሎት 3 |
450 |
28,000(ሀያ ስምንት ሺ ብር) |
26/01/2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፤የአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር፣የታክስ ክሊራንስ ያለው እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ https://epg.ppa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአየር ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በካሽ በመክፈል ወይም ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት/ EEU/ አካውንት ቁጥር 1000259834876 በማስገባት እና የባንክ ደረሰኝ በማምጣት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከመስከረም 11/2019 ዓ.ም አንስቶ እስከ መስከረም 26/2019 ዓ.ም ድረስ የጨረታው ሰነድ መውስድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የመወዳደርያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ መስከረም 26/2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን መስከረም 26/2019 ዓ.ም 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም በደብረማርቆስ ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የሪጅኑ ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡
5. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (+251 581 784 633) መደወል ይችላሉ፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረማርቆስ ሪጅን
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-06 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T09:14:31.000Z
- Source: 2merkato