Building and Finishing Materials
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት እየገነባቸዉ ላሉ ለደ/ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ለደ/ማርቆስ አዲሱ መናህሪያ፣ ለደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ግንባታ፣ ለፍ/ሰላም ከተማ ኮሪደር ልማት እና ለቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚዉል የቢትመን አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እየገነባቸዉ ላሉ ለደ/ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ለደ/ማርቆስ አዲሱ መናህሪያ፤ ለደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ግንባታ፣ ለፍ/ሰላም ከተማ ኮሪደር ልማት እና ለቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚዉል የቢትመን አቅርቦት ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ምድብ 1፡- ለደ/ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚዉሉ የቢትመን አቅርቦት
- ምድብ 2፡- ለደ/ማርቆስ አዲሱ መናህሪያ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የቢትመን አቅርቦት፣
- ምድብ 3፡- ለደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚዉሉ የቢትመን አቅርቦት፤
- ምድብ 4፡ ለፍ/ሰላም ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚዉል የቢትመን አቅርቦት
- ምድብ 5- ለቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ መንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚዉል የቢትመን አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 እና አዲስ አበባ 4ኪሎ አልማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤ ሆኖም የጨረታ ፖስታው ገቢ የሚሆነው አዲስ አበባ 4ኪሎ አልማ ህንጻ 5ኛ ፎት ላይ በሚገኘዉ የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው።
2) ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ አዲስ አበባ 4ኪሎ አልማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባችኋል።
3) ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤የጨረታ መክፈቻ ቀን በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
4) ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደስ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
5) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የጠ/ዋጋ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
6) አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል።
7) አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
8) አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፋቸዉን ቢትመኖች በራሱ ትራንስፖርት በየምድቡ በተጠቀሰው ፕሮጀክት መሰረት በማቅረብ ማስረከብ አለበት።
9) አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ቢትመኖች በባለሙያ ተረጋግጦ /ቴስት/ ማለፍ አለበት።
10) አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 / ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
11) ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ወይም በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ለደ/ማርቆስ በስልክ ቁጥር፡- 0920 514 407
ለአዲስ አበባ በስልክ ቁጥር 0955 274 444 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
በደ/ማርቆስ ከተማ/አስተዳደር መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቆይቶ በቀጣይ ቀን ከጥዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-10-09 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቆይቶ በቀጣይ ቀን ከጥዋቱ 3፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Menkorer Construction Enterprise
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T10:36:06.000Z
- Source: Qelal Tenders