Veterinary Equipment and Supplies
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሚ አ/ከ/አስ/ር ግብርና አካባቢ ጥበቃ እና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አገ/ት የሚውል የእንስሳት መድኃኒት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የገስጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሚ አ/ከ/አስ/ር ግብርና አካባቢ ጥበቃ እና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አገ/ት የሚውል የእንስሳት መድኃኒት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይቻላል።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
3. ከሚመለከተው አካል በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
5. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ንብ/አስ/ር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
6. የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ 5,000/አምስት ሺህ/ ብር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል።
9. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
10. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ በ3፡30 ሠዓት
- Bid opening: 2026-10-07 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሠዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Mizan Aman City Administration Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T10:49:34.000Z
- Source: Qelal Tenders