House Furniture

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፀዉን በ2019 በጀት ዓመት ለተቋሙ ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች /ዳይሬክተሬት / ሥራ ላይ የሚያስፈልግዉን ከታች የተዘረዘሩትን ማለትም፡-

1. ፈርኒቸርና የፈርኒቸር ዉጤቶች ቋሚ የቢሮ ቁሳቁስ /የተገልጋይ አግዳም

2. የጽዳት እና የቢሮ የዉበት ሥራ የሚዉል የተለያዩ ዕቃዎች

3. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የዲጅታላየዜሽን መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች Server dell; Desktop computer,Printer;Cisco2960-24/48/port

4. የጽህፈት መሳሪያ እስቴሽነር

5. የቢሮ ማናጀር ሶፋ፤ የማናጀር ወንበሮች

6. ጨርቃ ጨርቅ ለሆስፒታሉ ደንብ ልብስ የሚዉል

7. በየአስራ አምስት ቀን ወደ ይርጋዓለም ሆስፒታል ለስልንደር ለማስሞላት የመኪና ኪራይ

8. ሕትመትና የህትመት ዉጤቶች

9. የቧንባ ዕቃዎች

10. የመድኃኒትና የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ሬኤጀንቶች

11. ኤሌክትርክ መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች florcent lamp, electric wire, etc 

12. የሕክምና መሳርያ እና አክሰሰር መለዋወጫ /የሕክምና ማሽኖች እና ዕቃዎች ግልጽ የሀገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድም ተከተል ሁኔታዎችን ማሟለት ይጠበቅባቸዋል።

1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለዉ/ያላት

2. የዘመኑን ማለትም የበጀት ዓመቱን ግብር መክፈላቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችል እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው

4. ጨረታዉን አሸንፎ የሚያቀርበዉን ዕቃ ንብረት ጥራቱን ለማረጋገጥ ናሙና ማቅረብ የሚችል

5. ጨረታዉን ያሸነፉ ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት ዕቃዉን/ የንብረቱን እስከ ሆስፒታሉ በእራሱ ወጪ የሚያቀርብ

6. አሸናፊ ሆኖ የሚጠራዉ ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት የዕቃዉን የንብረቱን ጥራትና ደረጃ በጨረታ ሰነድ ላይ ሆስፒታሉ ባስቀመጠዉ መልኩ ውል ገብቶ በዉሉ መሰረት የሚያቀርብ

7. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ለተከታታይ ዘወትር የስራ ሰዓት እና ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን አ⁄ ዳይሬክተሮት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለዉ የዋጋ ማቅረቢያ ወይም በራሳቸዉ የዋጋ ማቅረብያ በግልጽ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታውን እንዲያስገቡና በተገለፀው ቀን የሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ⁄ድጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዘርፍ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በመስሪያ ቤቱ ስም ለቦና ሆስፒታል ማስያዝ ይኖርበታል።

10. ጨረታው የሚገባበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀናት ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ስዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ።

12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራቾች ከዉድድሩ ዉጭ ይሆናል። ማሳሰብያ ፡- ጨረታውን የሚገባበት መደበኛ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀንና ሰዓት ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር
09 26 38 48 50/ 09 16 40 15 99/
09 16 37 27 54/ 09 16 07 11 84 / 09 16 40 15 99 ደውሎ መረዳት ይችላል። 
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-10-10
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-10 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Bona General Hospital
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 23, 2026)
  • Posted at: 2026-09-23T08:43:16.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders