Vehicle and Machinery Sale
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Vehicle and Machinery SaleSales, Disposals and ForeclosureVehicle and Machinery Foreclosure
Addis Ababa
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ንብ/19/2018
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- የተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች ከመስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 10 ቀን 209 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በባንክ አካውንት ቁጥር ETB176400010001 የማይመለስ ብር 500.00(ብር አምስት መቶ ብቻ) ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰንጋተራ ኮሜርስ ፊት ለፊት ራስ አበበ አረጋይ መንገድ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ሰፕላይ ቼይን አስተዳደር መምሪያ 26ኛ ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ የገዙበትን ደረሰኝ እና ጨረታ ሰነድ በመያዝ የተሽከርካሪዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ሪቼ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ የወደፊት ግንባታ ቅጥር ግቢ እና አራት ኪሎ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ በመገኘት ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓም ከጧቱ 4:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት እንዲሁም በመጨረሻው ቀን ጥቅምት 10 ቀን2019 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ብቻ መጎብኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ያገለገለ ተሽከርካሪ ዓይነቱንና የሰሌዳ ቁጥር በትክክል በመጥቀስ የሚገዙበትን ዋጋ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት የባንኩ ሰፕላይ ቼይን አስተዳደር ቢሮ በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመላክ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ያገለገለ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ጋር መሆኑ አለመሆኑን በግልፅ በሰነዱ ላይ በጽሁፍ ማመልከት ይኖርባቸዋል፤ ይህንን በግልፅ ያልጠቀሱ ተጫራቾች ካሉ ያቀረቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ጋር እንዳቀረቡ ይወሰዳል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያያዘበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ ከውድድር ውጪም ይሆናል፡
- ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንፃ 26ኛ ፎቅ በሰፕላይ ቼይን አስተዳደር መምሪያ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ዝርዝር ውጤት በባንኩ እንደጸደቀ ለተጫራቾች ይገለጻል፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊ ተጫራቾች ባንኩ ውጤቱን እንዳሳወቀ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች ግን ላሸነፉበት ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያውን ከፍለው ንብረቱን ካነሱ በኋላ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፣
- አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ያገለገለ ተሸከርካሪዎች ማሸነፋቸው በፅሁፍ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያውን በመፈጸም ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤
- አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ባንኩ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ለቆየበት በየቀኑ ብር 500.00 ለሃያ ቀን የሚያስከፍል ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሱ ባንኩ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል፡
- አሸናፊ ተጫራቾች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያውን ከፍለው ንብረቱን ካልተረከቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
- ለጨረታ የቀረቡት ያገለገለ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ወጪ፣ የስም ማዛወሪያ፣ ለመንግስት የሚከፈሉ የታከስ ክፍያዎችና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊው ገዢው ይከፍላል፣
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-50-44-52 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0116296246/0115512650
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-10-20 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nib International Bank S.C.
- Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ ያገለገለ ተሽከርካሪ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 23, 2026)
- Posted at: 2026-09-23T09:10:37.000Z
- Source: Qelal Tenders