Spare Parts and Car Decoration Materials
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማና ከመነዳሪ ግዥ መግዛት ይፈልጋል
Description
የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማና ከመነዳሪ ግዥ
ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አሸጨ/0018ኦኩስፋ-2/2019 ዓ.ም
- በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የተለያዩመጠን ያላቸው ጎማና ከመነዳሪ ግዥ ጨረታ (የጎማዎች ዝርዝርና መጠናቸው በጨረታ ሰነድ ክፍል 6 የፍላጎት መግለጫ ላይ ተገልጸዋል) መግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ ፤ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መክፈቻ ትክከለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6:00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00–10፡30 እናቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፤ ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተጠቀሰው ነው፡- 5.1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነአ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ። ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85/ 0986862766/ 0940209464 አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የዕቃው ርከከብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪ ቢሮ ነው።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tel-0940209464
ኃይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ
Tel: 09-91-14-94-85/0986862766
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር‐2 ስኳር ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን
- Bid opening: 2026-10-10 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T08:15:38.000Z
- Source: Qelal Tenders