Materials
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡
- በመስኩ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- ዘመኑ ግብር የተከፈለበት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት መረጃ ያላቸው።
- ጥራት ያለው ዕቃ ማቅረብ የሚችሉና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና እና በፎቶ አስቀድሞ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዢ እና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ከብ ማህተም እና ፊርማ በታሸገ ኢንቭሎፕ ዉስጥ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት በገዙት ዝርዝር ሰነድ ላይ በግልፅ መፃፍ አለባቸው ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራጩ ፊርማውን ከአጠገቡ ማሰቀመጥ ግዴታ አለበት።
- ጨረታው ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምክትል ርዕሰ መምህር ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱን ዋጋ የሞላውን በጠቅላላ ድምር ላይ ማሰቀመጥ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቹ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከታክሲ ማዞሪያ ከፍ ብሎ የካ ኢንዱስትሪያ ኮሌጅ ፊት ለፊት
የሚገኝው ህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ስ.ቁ 01111400 80 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
p.o.box 20055
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-07 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hizebawi Serawit Kindergarten and Primary School
- Buyer address: ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወረዳ 02 የካ ኢንዱስትሪያል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ፊት ለፊት
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T08:36:50.000Z
- Source: Qelal Tenders