Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሰ/ፍ/ጤ/ጣ/ግ/ጨ/ 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ዕቤት የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ 2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሟሟላት ይኖርበታል።

1, የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች 2. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 3. የደንብ ልብሶች 4. ቋሚ ዕቃዎች 5. የጥገና የቧንቧ እና የኤሌክትሪከ ዕቃዎች 6. የህትመት ስራዎች 7. የተለያዩ የቢሮ ማስዋቢያ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን 8. የመኪና ጎማን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ 1(አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4 የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

6. በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 45 የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. መ/ቤቱ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ በክፍል 6 ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ላይ ናሙና/ሳምፕል/ እንድታቀርቡ በተጠየቀው መሠረት የተጠየቁትን ናሙና /ሳምፕል/ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 45 የግዥ የስ/ሂደት እንድታስገቡ እየገለጽን ናሙና (ሳምፕል) ያልቀረበባቸው እቃዎች ውድቅ እንደሚሆኑባችሁ አውቃችሁ ለምትወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ናሙና(ሳምፕል) እንድታቀርቡ እያሳሰብን የምታቀርቡትን ናሙና/ሳምፕል/ በተመለከተ ጤና ጣቢያው የራሱን ኮድ የሚሰጥ በመሆኑ በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ በተጨማሪም ከጽዳት ዕቃዎች የእጅ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ሶፍት፣ በረኪና፣ ዲቶል እና ኦሞ፣ ከቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች መካከል እርሳስ፣ እስኪርብቶ፣ ፍሉድ፣ ኡሁ፣ ማርከር እና የማህተም ቀለም የጤና ጣቢያው የጥራት ኮሚቴው ዕቃዎቹን ከፍቶ ጥራቱን የሚፈትሽ/የሚመረምር/ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል።

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኃል፡፡ ለእያንዳንዱ ሎት የምታቀርቡት CPO መጠን የእንደሚከተለው ይሆናል፡-

1. የደንብ ልብሶች 6211፡- 44,720.00 (አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ብር ብቻ)

2. አላቂ የቢሮ እቃዎች 6212 ፡- 47,000.00 (አርባ ሰባት ሺህ ብር ብቻ)

3. የተለያዩ የህትመት ስራዎች 6213 ፡- 20,968.27 (ሀያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት ብር ከ 27/100 ሳንቲም

4. አላቂ የጽዳት ዕቃዎች 6218 ፡- 51,000.00 (ሀምሳ አንድ ሺህ ብር ብቻ)

5. የጥገና እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 6219 ፡- 11,000.00 (አስራ አንድ ሺህ ብር ብቻ)

6. ቋሚ ዕቃዎች 6313 ፡- 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር ብቻ)

7. የተለያዩ የቢሮ ማስዋቢያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች 6314፡- 6,000.00 (ስድስት ሺ ብር ብቻ)

8. የመኪና ጎማ 6241 ፡-14,849.88 (አስራ አራት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከ ሰማኒያ ስምንት ሳንቲም)

10. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ።

11. የጨረታው ዋጋ ለ2 ወር ጸንቶ ይቆያል ይህም ሲሆን ገዥና ሻጭ ተስማምተው እስከ ቀጠሉ ድረስ ለ6 ወራት ድረስ በስምምነት ይቆያል።

12. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ መቅረብ አለባችሁ።

13. ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም።

14. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማዓረብ ይጠበቅባቸዋል፡ : የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ/ ጀምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ፣ የወል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።

15. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ ጤና ጣቢያው የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል።

16. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቹሉም፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል።

17. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጤና ጣቢያው ግቢ ቢሮ ቁጥር 45 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ይታሸግና በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።

18. በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማው እኩል ውጤት ካቀረቡ ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ አምራች ለሆኑ ዕድሉን የምንሰጥ ሲሆን የሀገር ውስጥ አምራች ተወዳዳሪ ካሌለ አሸናፊውን በእጣ የምንለይ ይሆናል።

19. አሸናፊ ተጫራች የግዢ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ ከደረሰው ከ5ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት ውል ከግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት፡፡ የውል ግዴታ ካልተወጣ በቀጣይ ከመንግስት ግዢ እንዲታገድ ይደረጋል።

20. ገዢው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን /ብዛት/ላይ 20% ከውል በፊት የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።

21. አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በክፍል 8 በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረክብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ 10% መ/ቤቱ ይወርሳል።

22. በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል።

23. በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሜ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም በተሰጠው ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኃላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም።

24. በውድድር ወቅት በአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በአንዱ ዋጋ መሰረት እና በአሃዝና በፊደል በሚገለጽበት ወቅት ልዩነት ቢኖር በፊደል በተገለጸው መሰረት በማስተካከል ይገመግማል።

25. ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና/ሳምፕል/ በሚመረመርበት ወቅት በራሱ ተፈጥሮ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ መ/ቤቱ ካሳ አይከፍልም።

26. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስትርት/ወጪ/ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

27. በጨረታው ሠነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዩች አስመልከቶ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ በጽሁፍ ሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 45 በአካል በመምጣት ማቅረብ /መጠየቅ/ ትችላላችሁ።

28. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አቃ/ቃ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሠላም ፍሬ ት/ቤት አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0114 340 351

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-07 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Kality Sub City Selam Fire Health Bureau
  • Buyer address: አቃ/ቃ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሠላም ፍሬ ት/ቤት አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
  • Posted at: 2026-09-25T09:35:56.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders
Could not load content