Vehicle and Machinery Sale

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ዘመናዊ የልብስ ስፌት እና የጥልፍ ማሽነሪዎች በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የሁለተኛ ደረጃ ድር ድር ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ፣

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት አሰጣጥ ለዮሴፍ እና ሀይሉ የልብስ ስፌት ሽርክና ማኅበር በኪራይ አስተላልፎለት የነበረው ዘመናዊ የልብስ ስፌት እና የጥልፍ ማሽነሪዎች ተከራዩ በካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት የሚጠበቅበትን የማሽን ኪራይ ከፍያ በወቅቱ መከፈል ባለመቻሉ ባንኩ በካፒታል ዕቃ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/98 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 807/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የካፒታል ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ መልሶ በመረከብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የካፒታል ዕቃዎች በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

 

በድርድር ሽያጭ የሚሸጠው የሚከራየው ንብረት ሁኔታ

ብዛት

 

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

የድርድር ሽያጭ ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

የጨረታው ዓይነትና ደረጃ

 

የድርድር ሽያጭ ጨረታ የሚካሄድበት ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት

የካፒታል ዕቃዎች ዝርዝር

ዓይነት

1

2 Needle,4 Thread Over Lock Machine Full Set

Kansai

 

2

ጎንደር ከተማ አስተዳደር ፣ ማራኪ ክ/ከተማ ፣ ቀበሌ 18 ከሚገኘው የመንግስት ሸድ ውስጥ

 

8,516,045.93

 

የሁለተኛ የድርድር ጨረታ

 

ጥቅምት  17 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሚገኘው ቢሮ

 

2

Embroidery Machine (4 Heads) Full Set

Tajima

 

1

3

Tread Trimmer Machine

Unison

1

4

Richpeace Pure Chenille Embroidery Machine (2 Heads) Full Set

Richpeace

2

5

Upper and Lower Integrated Feed Pleating Lockstitch Machine

Richpeace

7

6

Computer Control High Speed Straight Button Hole Sewing Machine

Richpeace

1

7

Direct Drive Nailing Machine/button sewing

Richpeace

1

8

Iron Boiler Machine

Richpeace

1

የድርድር ሽያጩ ዝርዝር መመሪያ፡-

1. ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰቦች፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የሚገዛበትን ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በማዘጋጀት በዲስትሪክቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት የሚገዙበትን ዋጋ እና የግዥ ሁኔታ በመግለጽ ለዚሁ በተዘጋጀ ፖስታ ውስጥ በማሸግ እና በባንክ በተረጋጋጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በመቅረብ መደራደር ይቻላል።

2. የድርድር ሽያጭ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፤

3. የጨረታው አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ክፍያዎች በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።

4. መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠበቁ አሸናፊው ተጫራች በተደራደሩበት ባቀረቡት የድርድር ዋጋ ላይ 15% VAT/ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ጨምሮ መከፈል ግዴታ አለባቸው።

5. ባንኩ አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ዋጋ ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መከፈል የሚኖርበት ሲሆን ገንዘቡን በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ባንኩ የድርድር ጨረታ ሂደቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

6. በድርድር ጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በባንኩ ማህተም ተረጋግጦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

7. አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20 %(ሃያ በመቶ) በቅድሚያ በመክፈል በ15 ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟለት የማሽነሪ ኪራይ የዱቤ ግዥ ውል መፈረም ይኖርበታል። ነገር ግን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

8. ንብረቶችን ከጨረታ ቀን በፊት በአካል ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከባንኩ ጋር ፕሮግራም መያዝ ይኖርባቸዋል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም

በስልክ ቁጥር 058 221 0221/ 058 211 0184 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-27 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T07:46:44.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders