Spare Parts and Car Decoration Materials
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ዕቃ (Spare part) ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ዕቃ (Spare part) ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክሰ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ከስቶክ ያለውና ውል ገብቶ በተባለው ጊዜ ውስጥ የመኪና ዕቃ (Spar part) ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ / በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ዋጋ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንትኦርጅናልና ኮፒውንየፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውንቴክኒከልዶክመንትና CPO በተለያየ በአምስት (5) በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።
09 10 62 27 00/ 09 19 51 99 51/ 09 46 65 33 04/ 09 49 44 57 2/
አድራሻ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 13:00
- Bid opening: 2026-10-12 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Land Bureau
- Buyer address: ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ከዋናው አስፋልት 200 ሜትር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T07:55:10.000Z
- Source: Qelal Tenders