Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 02 ት/ጽ/ቤት የጋራ ጉሪ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፋልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 02 ት/ጽ/ቤት የጋራ ጉሪ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ እቃዎች ማለትም

  • ሎት 1.የትምህርት እቃዎች፣
  • ሎት 2. የቢሮ እቃዎች፣
  • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 4. የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 5. ፈርኒቸሮች ፣
  • ሎት 6. ፕላንት ማሽነሪ፣
  • ሎት 7. የላብራቶሪ ግብዓቶች፣
  • ሎት 8. የህክምና እቃዎች፣
  • ሎት 9. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 10. የህትመት ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፋልጋል።

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:

  1. ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
  2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው።
  3. የዘመኑን ግብር ስለመክፍላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፊኬት ያላቸው።
  6. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ድረ-ገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጀው ክፍል የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  7. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በመለየት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።
  8. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ በየሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን ገንዘብ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    • ሎት 1. የትምህርት እቃዎች፡- 50,000
    • ሎት 2. የቢሮ እቃዎች፡- 50,000
    • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፡- 50,000
    • ሎት 4. የደንብ ልብስ፡- 60,000
    • ሎት 5. ፈርኒቸሮች፡ 70,000
    • ሎት 6. ፕላንት ማሽነሪ፡- 80,000
    • ሎት 7. የላብራቶሪ ግብዓቶች፡- 50,000
    • ሎት 8. የህክምና እቃዎች፡- 10,000
    • ሎት 9. ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን፡- 15,000
    • ሎት 10. የህትመት ስራዎች፡- 20,000

 የኢትዮጵያ ብር በባንክ የከፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት።

1.1 ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘገጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ከት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 05 የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛት የሚጫረቱበት ዋጋ በሰነዱ ላይ በግልፅ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦሪጂናል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።

1.2 የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን በ11ኛው 3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ታሸጎ በእለቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ /ህጋዊ ወኪል ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽዕኖ አያመጣም፡፡

1.3 ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

1.4 ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

1.5 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማስገባት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

1.6 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቡት እቃ በናሙናው መሰረት ካልሆነ ተቀባይነት የለውም።

1.7 በዋጋ መሙሊያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡

2. ጋራ ጉሪ 2ኛ/ደ/ት/ቤት በግልጽ ጨረታ የተለያዩ የጽዳት እቃ፤ የትምህርት እቃዎች፣ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ፕላንት ማሽነሪ፣ ፈርኒቸሮችና፣ የላብራቶሪ ግብዓቶች፣ የህክምና እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና ህትመት ስራዎችን በሠንጠረዥ በቀረበው መሰረት የምትጫረቱበትን ዋጋ ቫትን በመጨመር ሞልታችሁ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የት/ቤቱ አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ o2 አያት ደራርቱ አደባባይ ሄልቦቴም ሪል ስቴት አጠገብ።

የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- +251118931482

በለሚ ኩራክ/ከተማ በወረዳ 02 ት/ጽ/ቤት የጋራ ጉሪ 2ኛ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ 3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል)
  • Bid opening: 2026-10-09 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በእለቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት)
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gara Guri Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T08:16:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders