House, Building and Warehouse
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ለጥልፍና ስፌት (ጋርመንት) እና ለካፌና ሬስቶራንት አገልግሎት የሚሆን የንግድ ቤቶች በግልጽ ጨረታ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ
ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግጨ 001/2019
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ባለው ይዞታ ለጥልፍና ስፌት (ጋርመንት) እና ለካፌና ሬስቶራንት አገልግሎት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የአንድ ካሬ ሜትር የኪራይ ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ሲሆን ከአንድ የኪራይ ቤት ቁጥር በላይ መጫረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
- ከ6 (ስድስት ) ወር ለበለጠ ጊዜ ያሸነፈበትን ገንዘብ ቅድሚያ ለሚከፍል ተከራይ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
- ተከራይና አከራይ በሕጉ መሠረት ውል ይዋዋላሉ፡፡
- በጨረታ ያሸነፉበትን ቦታ ቤት ለሌላ ማስተላለፍ፣ ማከራየት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ለካፌና ሬስቶራንት ኪራይ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለጥልፍና ስፌት (ጋርመንት) ከ25 ካሬ ሜትር በታች ለሆኑ የኪራይ ቤቶች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከ50 ካሬ ሜትር በላይ ለሆነ የኪራይ ቤቶች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በሽሮ ሜዳ ሽያጭ መደብር ሰነድ በመግዛት ተጫራቾች በአካል የኪራይ ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው ሽያጭ መደብር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከዋና መግቢያ በር ጀምሮ ማዕከሉ ለ3 ብሎኮች የተከፈለ እና ሦስት ዓይነት አገልግሎት እንዲሰጡ የተወሰነ ሲሆን እነርሱም፡-
9.1. ብሎክ 1 ለጥልፍና ስፌት (ጋርመንት) እና
9.2. ብሎክ 2 ለካፌና ሬስቶራንት አገልግሎት ለኪራይ የሚውል መሆኑን በመረዳት መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
10. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን የንግድ ቤት አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ቀናት ውስጥ ውል በመያዝ በራሱ ወጪ አድሶ አሳምሮ ወደ ሥራ መግባት አለበት::
በድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡- 0917-77-22-65/0913-07-74-86/0911-04-32-12
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር ገባ ብሎ ወይም FAO አጠገብ እና ሽሮ ሜዳ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ሽያጭ መደብር፣
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-12 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Education Materials Production and Distribution Organization
- Buyer address: አ/አ/ ቦሌ ክ/ከ ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ሆሊሲቲ ህንጻ ጐን በFOA እና በILRI ድርጅቶች መካከል 100 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ይገኛል
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T09:23:19.000Z
- Source: Qelal Tenders