House Furniture

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኮሚሽን ለ2019 በጀት ዓመት ኤክዚቪሽንና ባዛር ፕሮግራሞች ደረጃውን የጠበቀ የድንኳን፣ የዲጄ እና የሙዚቃ ባንድ ከነሙሉ ሳውንድ ሲስተሙ እና ሌሎችንም እቃዎች በኪራይ አገልግሎት ግዥ ለአንድ ዓመት የአገልግሎት ግዥውን አወዳድሮ መጠቀም እና የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አአህስኮ/ ብግጨ /አግ/002/2019

የኤግዚብሽንና ባዛር አገልግሎት ግዥና የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኮሚሽን ለ2019 በጀት ዓመት ኤክዚቪሽንና ባዛር ፕሮግራሞች ደረጃውን የጠበቀ የድንኳን፣ የዲጄ እና የሙዚቃ ባንድ ከነሙሉ ሳውንድ ሲስተሙ እና ሌሎችንም እቃዎች በኪራይ አገልግሎት ግዥ ለአንድ ዓመት የአገልግሎት ግዥውን አወዳድሮ መጠቀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ መሰፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ተ.ቁ

የሚገዛው እቃ (አገልግሎት) አይነት

የሎት ምድብ

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

1

ለኤክዚቭሽንና ባዛር ፕሮግራም እቃዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ

ሎት አንድ

50,000

2

የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ

ሎት ሁለት

10,000

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT5%)፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር ለመክፈሉ ታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በአንድ ፖስታ ጨረታ አንዲወዳደሩ እየጋበዘ የተጫራቾች መወዳደሪያ መስፈርትና ሁኔታዎችን እንደሚከተለው ቀርበዋል።

1. በጨረታው የሚወዳደሩት አገልግሎት አቅራቢዎች ለኤክዚቭሽንና ባዛር ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት በታቀደው መሰረት የሚዘጋጅላቸው ቦታ ድረስ ሄደው አገልግሎቱን በራሳቸው ወጭ ገጥመውና ሰረተው ማዘጋጀት አለባቸው።

2. ኮሚሽኑ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የአገልግሎቱን ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እስከ ፕሮግራሙ መጨረሻ አንድዓመት ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታዎቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከኮሚሽኑ 3ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማግኝት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት በሲፒኦ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንከ ዋስትና (Addis Ababa City Administration Cooperative commission) በማለት በማሽግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በኮሚሽኑ 3ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ሕዝባዊ ወይም ኃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል።

6. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው 

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ መስከረም ማዞሪ ተብሎ በሚጠራው ቴሌ ጋራጅ አካባቢ ከሚገኘው ካሮጋ ፋርማ ህንፃ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-126-36-93

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Workers Union Corporation
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T09:36:39.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders