Spare Parts and Car Decoration Materials

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና የሥልጠና ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ በማዕከሉ ለሚያሠለጥናቸው ሠልጣኞችና አሠልጣኞች የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና የሥልጠና ቁሳቁሶች የክልሉ መንግሥት ባወጣው የግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 በመከተል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች፡-

ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ እስፓርት ትጥቆች የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ ዶክመንት የማይመለስ አንድ መቶ (100) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የተጫራቾች ግዴታ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ከሆኑ፤ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታደሰ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5.  ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የኢትዮጵያ ብር 1% በCPO በ ሲንቄ ባንክ በማስገባት ፣ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በአቅራቢነት የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮፒና ዋናውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት 16/1/2019 እስከ 6/2/2019 ዓ.ም. ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሠልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ ፡፡
  8. ከላይ በተገለጸው መሥሪያ ቤት አድራሻ ውስጥ በ16ኛው ቀን በ9/2/2019 ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት( ባይገኙም) በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9.  አሸናፊው ድርጅት ማናቸውንም አስፈላጊ ወጪዎች ችሎ ያሸነፈባቸውን የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች በሰዓቱ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  10. ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-

0112609010፣0913286868 ወይም  112602341

አምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-19 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ambo Football Training Center
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T09:46:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders