Materials

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ለአገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ዐ1/2019

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ለአገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  2.  አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  3. የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቆች
  4.  ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መፅሐፍት
  5.  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  6.  ቋሚ ዕቃዎች

በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ለውል ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) 10 % ዋስትና ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 300 (ሶስት መቶ) የማይመለስ በመከፈል መግዛት የሚችል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል ቫትን ጨምሮ ተሞልቶ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO) ደግሞ በጨረታው ኦርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ወይም እሴት ጨምረው ለሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ ዕቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚመጡ ነጋዴዎች የተሰማሩበትን ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12.  ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ት/ቤቱ ሰነድ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  13. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ተዘግቶ በዛው እለት 4:30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
  14. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ከንግድ ማተሚያ ጀርባ (ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አሮጌው ቄራ በሚወስደው መንገድ ከሜሪስቶፕስ ትንሽ ገባ ብሎ)

ስልክ ቁጥር 0118548084

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ ት / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: John F. Kennedy No. 1 Kindergarten and Elementary School
  • Buyer address: አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ከንግድ ማተሚያ ጀርባ ( ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አሮጌው ቄራ በሚወስደው መንገድ ከሜሪስቶፕስ ትንሽ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T10:14:27.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders