Office Furniture

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ለፈርኒቸር ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፈርኒቸር ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ልዩ ልዩ የፈርኒቸር ግብዓቶች ግዥ ግልጽ

ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/03/2019

ድርጅታችን ለፈርኒቸር ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፈርኒቸር ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

1. በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን።

2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሣሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።

5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የድርጅቱ አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ Tel /011 646-3481 መረጃ ማግኘት ይቻላሉ።

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-08 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Education Materials Production and Distribution Organization
  • Buyer address: አ/አ/ ቦሌ ክ/ከ ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ሆሊሲቲ ህንጻ ጐን በFOA እና በILRI ድርጅቶች መካከል 100 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ይገኛል
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 600.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T10:44:49.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders