Plastic Products

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ. አሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ብዛቱ 400,000 (አራት መቶ ሺህ) የሆነ የብቅል ምርት ማሸጊያ ከረጢት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን አምራች ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ NCB/OACFLID/AMF/15/2018

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ብዛቱ 400,000 (አራት መቶ ሺህ) የሆነ የብቅል ምርት ማሸጊያ ከረጢት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን አምራች ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ)።

  • ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት በኃላ 7፡00-10፡00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ-ቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ወይም Bank Guarantee ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ፖስታቸውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርት መስረት ሶስት ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባችዋል።

6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡-

  • ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ 7ኛ ፎቆ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡

7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 09-65-65-04-81 / 09-65-65-02-85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-17 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Oromia Agricultural Cooperatives Federation Ltd Assela Malt Factory
  • Buyer address: Assela
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T10:48:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders