Accounting and Auditing, Accounting System Design
መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት ዓመታት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል
Description
የፐብሊክ ኦዲተር የሥራ ጨረታ
መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት በቅርብ ጊዜ የፋይናንስ ዘርፉን የተቀላቀለ ተቋም ሲሆን፤ፍላጎት ያላቸውን የፐብሊክ ኦዲት ድርጅቶች ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት ዓመታት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል::
በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
1. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የፐብሊክ ኦዲተር ፍቃድ የተሰጣቸው ተቋማት ብቻ፤
2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
3. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተቋም፤
4. በሥራው ላይ በተለይም የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው፤
5. የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል፤
6. አዲሱ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ /DIRECTIVE NO.MFI/37/2024/ መስፈርትን የሚያሟላ የኦዲት ተቋም፤
7. የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከ2019-2021 ዓ.ም ድረስ ያለው የሶስቱንም ዓመት ያካተተ መሆን ይኖርበታል::
8. መባዕ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋናው መስሪያ ቤታችን አራትኪሎ ቅድሥት ሥላሴ ዩንቨርሲቲ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2-13 በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን TOR እና የጨረታ ሰነድ በተጠቀሱ ቀናት ዋናው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 251-928-010-203 ወይም 251-929-010-203
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-03 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር
- Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T14:49:28.000Z
- Source: Qelal Tenders