Vehicle and Machinery Foreclosure

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፀባ/006/2018

ፀሐይ ባንክ አማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

የተሸከርካሪዎቹ ዝርዝር መረጃ

ተ.ቁ

የሞዴሉ አይነት

መጠን

ብዛት

የተመረተበት ዓ.ም እና ሃገር

1

Hyundai Tucson

ቁጥር

04

2021/Korea

1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች በቅሎቤት አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ3፡00-5፡30 ከሰዓት ከ8፡00-10፡30 መመልከት ይችላሉ።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓም እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2019ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ፀሐይ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ላይ በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር 1000033657 ግቢ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንያንዱ ተሽከርካሪዎች በተናጥል የመነሻ ዋጋውን 2% ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በፀሐይ ባንክ አማ ስም በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከአንድ በላይ ተሸከርካሪ መጫረትና መግዛት ይችላሉ።

4. ጨረታው ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በባንኩ ዋና መስሪያቤት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ የሚከፈት ይሆናል።

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለዉ የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ዋናዉንና ቅጂዉን በተለያዩ ፖስታ በማሸግና ሁለቱን (የዋና እና ቅጂ ፖስታ እሽጎች) በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ ዉስጥ አድርገው በማሸግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉትን ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያ በመክፈልና የአሸናፊነት መግለጫ ደብዳቤ ከባንኩ ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በ10 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ መኪናውን መረከብ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ያልከፈለ ተጫራች ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

7, በጨረታው ተሳትፈው ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8 የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዛወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0114 705 613 / 0114 706 033 ይደውሉ!


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-10-16 15:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsehay Insurance S.C.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T15:34:56.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders