Building and Finishing Materials

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በክልሉና በከተማዉ በጀት ድጋፍ በከተማዉ ውስጥ የቢሮ የህንፃ ግንባታ G+3 ቀሪ ስራዎች ለማስጨረስ የጉልበት የእቃና የማሽነሪ ግዥዎችን ጨምሮ መስፈርቱን የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በክልሉና በከተማዉ በጀት ድጋፍ በከተማዉ ውስጥ የቢሮ የህንፃ ግንባታ G+3 ቀሪ ስራዎች ለማስጨረስ ፓኬጅ ቁጥር AM DEJEN/CP/CW/07/2020/2021 lot2 የጉልበት የእቃና የማሽነሪ ግዥዎችን ጨምሮ መስፈርቱን የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።

3. የግንባታ ግዥው ወይም ዋጋው ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. GC/ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ እና BC ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ወደ ፋይናንሽያል ለማለፍ ቢያንስ 70 በመቶ የቴክኒካል  ዶክመንት ውጤት ማምጣት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. የስራዉ ዝርዝር መግለጫ ከተዘጋጀው /SBD/ የተጫራቾች መመሪያ ማግኘት ይችላሉ።

7. የግንባታ ተጫራቾች እያንድንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,200 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከደጀን ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ25 ቀናት ማግኘት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1,600,000 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

9. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ።

10. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የቴክኒካልና ፍይናንሻል ዶክሜንት በጥንቃቄ በታሸገ የተለያየ ፖስታ በፖስታው ላይ አድራሻውን በመፃፍ ደጀን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 26ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ 3፡50 ይታሽጋል።

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 18 በ26ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 0024 / 058 776 1009 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-23
  • Bid closing time: 09:50
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛዉ ቀን ከረፋዱ 3፡50 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-23 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dejen City Administration F/E/D/B
  • Bid bond: 1,600,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Be'kur (Sep 28, 2026)
  • Posted at: 2026-09-29T09:06:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders