Spare Parts and Car Decoration Materials
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢፕ.ድ 007/2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. የመኪና መለዋወጫ (በድጋሚ የወጣ)
2. አድቫንስ ዲስክቶፕ
3. የቆሎ የውሃና ቡና
4. የውሃ ማጣሪያ (በድጋሚ የወጣ)
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የንግድ ምዝገባ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
- የቫት ሰርተፍኬት
- በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
ሎት-1 የመኪና መለዋወጫ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 254,503.60 ( ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሶስት ብር ከ60/100 ሳንቲም)
ሎት-2 አድቫንስ ዲስክቶፕ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 120,000.00(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር)
ሎት-3 የቆሎ የውሃና ቡና የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር)
ሎት- 4 የውሃ ማጣሪያ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር)
በሲ.ፒ.ኦ፣ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ
ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Bid opening: 2026-10-14 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 29, 2026)
- Posted at: 2026-09-29T09:10:00.000Z
- Source: Qelal Tenders