Consumable Goods
በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እቃዎችን በሃራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ሐራጅ ቁጥር 08/2019
በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)፣ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አዳዲስ አልባሳት፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል የቧንቧ እቃዎችን) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፦ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይመመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን።
1, ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ ዮበትን ደረሰኝ ጨምሮ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ ሰነዱን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቀበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የጨረታው አይነት |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን |
ስልክ ቁጥር
|
|
1 |
ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
2 |
ኮስሞቲክስ |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
3 |
የኮንስትራክሽን ማቴሪያል |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
4 |
የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማቴሪያል(ቧንቧ እቃዎች |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
5 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
6 |
አዳዲስ አልባሳት |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
7 |
የተሸከርካሪ መለዋወጫ |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
8 |
የቢሮ መገልገያ እቃዎች |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019 |
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
|
9 |
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች |
ሃራጅ |
20/01/2019 |
25/01/2019
|
4፡00 |
26/01/2019 |
0221118429/0222118925 |
5. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
6. በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 1 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 33,300.00 ብር፣ ለምድብ 2 ኮስሞቲክስ 406,400.00 ብር፣ ለምድብ 3 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል 213,500.00 ብር፣ ለምድብ 4 ኮስሞቲክስ 849,300.00 ብር፣ ለምድብ 5 ኮስሞቲክስ 204,500.00 ብር፣ ለምድብ 6 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(ቧንቧ እቃዎች) 219,400.00 ብር ፣ ለምድብ 7 ኤሌክትሮኒክስ 119,100.00 ብር፣ለምድብ 8 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 127,100.00 ብር፣ለምድብ 9 ኮስሞቲክስ 15,000.00 ብር፣ለምድብ 10 አዳዲስ አልባሳት 37,300.00 ብር፣ ለምድብ 11 ኮስሞቲክስ 2,500.00 ብር፣ለምድብ 12 ኤሌክትሮኒክስ 44,500 ብር፣ ለምድብ 13 ኤሌክትሮኒክስ 60,300.00፣ ለምድብ 14 ኮስሞቲክስ 16,700.00 ለምድብ 15 ኮስሞቲክስ 22,300.00 ብር፣ ለምድብ 16 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 4,100.00 ብር፣ ለምድብ 17 የተሽከርካሪ መለዋወጫ 500.00 ብር፣ ለምድብ 18 የተሽከርካሪ ጎማዎች 4,100 ብር፣ለምድብ 19 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 61,600.00 ብር፣ለምድብ 20 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 17,200.00 ብር፣ ለምድብ 21 የቢሮ መገልገያ እቀዎች 1,800.00 ብር ለምድብ 22 የቢሮ መገልገያ እቃዎች 2,300.00 ብር፣ ለምድብ 23 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(Plastic tile spacers) 250,600.00 ብር፣ ለምድብ 24 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች 25,000.00 ብር፣ ለምድብ 25 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች 25,000.00 ብር፣ብር፣ ለምድብ 26 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች 25,000.00 ብር እና ለምድብ 27 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች 25,000.00 ብር በ (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
7. በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አከባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማየት እና መጫረት ይቻላል።
8. በሃራጅ ጨረታ እቃዎቹ የመነሻዋጋያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
11. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
☞ NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራቾች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙትን ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግና እቃው በድጋሚ ጨረታ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች
0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): 25/01/2019፣ 4፡00
- Bid opening: 2026-10-06 10:00
- Bid opening (note): 26/01/2019
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Sep 30, 2026)
- Posted at: 2026-09-30T09:18:03.000Z
- Source: Qelal Tenders