Accounting and Auditing, Accounting System Design

እሰይ ኃ/የተ/መሰ/ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የ2017 እና የ2018 በጀት ዓመት ሂሳብ በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

እሰይ ኃ/የተ/መሰ/ቁጠባናብድር ህብረት ሥራ ማህበር የ2017 እና የ2018 በጀት ዓመት ሂሳብ በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆናቹን እየገለጽን ተሳታፊዎች ማሟላት ያለባቸው፡-

1. ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ የጸና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እና የስራ ፍቃድ ያሳደሰ፤

2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል

3. የግብር ከፋይ ምዝገባ እና ሰርተፊኬት /TIN/ ያላቸው።

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ፤

5. የዘመኑን የስራ ግብር ስለመክፈሉ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል

6. በህብረት ሥራ ኦዲት ላይ የተረጋገጠ ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል።

7. ከህብረት ስራ ማህበሩ አባል ያልሆኑና የጥቅም ግጭት የሌለባቸው።

8. በቂ ሙያዊ ብቃት እና በህብረት ሥራ ማህበራት የኦዲት ሥራ ልምድ ያላቸው ሠራተኞች ስለመኖራቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

9. ከፍተኛ ጥራት ያለው የኦዲት አገልግሎት በማቅረብ ረገድ ጥሩ የስራ መዝገብ ያለው

10. በኦዲት ሙያ ቢያንስ ሁለት አመት የሰራ

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት አዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 መገናኛ ማራቶን ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 416 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል በመገኘት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ህብረት ስራ ማህበሩ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-09 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: እሰይ ኃ/የተ/መሰ/ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 30, 2026)
  • Posted at: 2026-09-30T11:56:13.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders