Equipment and Accessories

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨቁ 03/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ዘርፍ

የጨረታው ዓይነት

እቃው ያለበት ቦታ

1

ኤሌክትሮኒክስ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

2

ኮስሞቲክስ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

3

ጫማ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

4

የእጅ ሰዓቶች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

5

ልዩ ልዩ ዕቃዎች

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

6

ፓኪንግ ማሽን

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

7

መለዋወጫዎች

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

8

ጫማ

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

9

ኤሌክትሮኒክስ

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግስት መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500ሺ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም። በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መከፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
  2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00 5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው መለዋወጫዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ጫማ (ምድብ ዐ1) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፤ጫማ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ ኤሌክትሮኒክስ 20,000 (ሃያ ሺ ብር)፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 10,000(አስር ሺ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና(CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ግልጽ ጨረታ

እስከ 27/01/2019

28/01/2019 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል

2

ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

ሐራጅ ጨረታ

እስከ 27/01/2019

28/01/209 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

5. ጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በሰመራ : ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ - ሙሉ መብት አለው።

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡- 033 240 1510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-08 10:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
  • Posted at: 2026-10-02T07:54:12.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders