House Furniture
የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉትን በዋናነት የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን (ፈርኒቸር እና ኤክትሮኒክስ) እና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጥገና ሥራዎችን እና የጥገና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በምድብ (በሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - አ/ጤ/ጣ - 001/2019
የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉትን በዋናነት የጽኅፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን (ፈርኒቸር እና ኤክትሮኒክሰ) እና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጥገና ሥራዎችን እና የጥገና ኤሌክትሮኒክሰ ዕቃዎች በምድብ (በሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጽኅፈት መሳሪያዎችን፣ የደምብ ልብሶችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን፣ ህትመቶችን እና ሌሎች የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን፣ የጥገና ሥራዎችን እና የጥገና ኤሌክትሮኒክሰ ዕቃዎች ሥራዎችን በጥራት ለማቅረብ ወይም ለመሥራት የሚያስችል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የ2019 ዓ.ም የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ ድህረ-ገጽ ላይ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በግልጽ የሚታይ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነጻ ስለመሆናቸው መልቀቂያ (ክሊራንስ) እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የሲፒኦ ሰነድ /ብር 11,000.00/ አስራ አንድ ሺህ ብር/ በአዋሬ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (ሲፒኦ) ብቻ ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የሲፒኦ ሰነድ በኦሪጅናል ሰነድ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል።
8. ጥቃቅን እና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ እና በራሳቸው በሚያመረቱት ዕቃዎች ላይ ብቻ ካደራጃቸው ተቋም ለመስ/ቤታችን የዋስትና ደብዳቤ ከሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
9. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
10. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ እንጂ በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም።
11. ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ሳይሰርዙ፣ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ ለተጠቀሰው አገልግሎት ወይም ዕቃ ዋጋውን ብቻ በዋጋ መሙያው ላይ መሙላት አለባቸው፤ ይህን ያላደረገ ተጫራች ከጨረታ ውድድሩ ይሰረዛል።
12. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት /VAT/ ማካተት አለባቸው።
13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደርያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።
14. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞላው ነጠላ ዋጋ ነው።
15. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዋሬ፣ አዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊትለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118 688 278 ደውሉው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የአዋሬ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-14 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Aware Health Post
- Bid bond: 11,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
- Posted at: 2026-10-02T07:57:06.000Z
- Source: Qelal Tenders