House, Building and Warehouse
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባው አዲስ አፓርትመንት ህንፃ በሙሉ (ሙሉ ህንፃውን) ማከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የአፓርትመንት ህንፃ ከራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባው አዲስ አፓርትመንት ህንፃ በሙሉ (ሙሉ ህንፃውን) ማከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
የሕንፃው ዝርዝር መግለጫ
- አድራሻ ካዛንቸስ፣ አዲስ አበባ
- የወለል መጠን ምድር ስር 2 ወለል (B+2) + ሜዛኒን + ምድር + 18 ወለል (G+18)
- የመኖሪያ አፓርትመንቶች (በአጠቃላይ 150 ክፍሎች)
- ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት፡ 24 ክፍሎች
- ባለ 2 መኝታ አፓርትመንት፡ 42 ክፍሎች
- ባለ 1 መኝታ አፓርትመንት፡ 48 ክፍሎች
- ስቱዲዮ (Studio) አፓርትመንት 36 ክፍሎች
ተጨማሪ አገልግሎቶች
- የራሱ ግቢ ያለው (Own Compound)
- ጄኔሬተር (Standby Generator)
- መኪና ማቆሚያ የሚሆኑ 2 ምድር ወለሎች (B+2 underground Parking)
- በግራውንድ እና ሜዛኒን ወለሎች ላይ ለቢሮ፣ ለንግድ፣ ለባንክ ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሰፊ ቦታዎች
የመወዳደሪያ መስፈርቶች
- ተወዳዳሪዎች ህጋዊ የድርጅት ምዝገባ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተቋማት ሙሉ ህንፃውን ለመከራየት የሚያስችላቸውን የፋይናንስና የቴክኒክ ፕሮፖዛል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች የታዘዘውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- መረጃና የቦታ ጉብኝት፡- ፍላጎት ያላቸው አካላት የህንፃውን ዝርዝር ፕላን ለመመልከት፣ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ እና ህንፃውን በአካል ተገኝተው ለመጎብኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታተይ ስራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ሂልተን ሆቴል ፊት ለፊት አዲሱ ህንፃ 3ኛ ወለል፣ ስልክ ቁጥር ፡-
+25111 553 1782/+251930470796/+251978738565
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Tender details
- Deadline: 2026-10-14
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታተይ ስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-14 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ministry of Foreign Affairs
- Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T07:16:07.000Z
- Source: Qelal Tenders