Water Pipes and Fittings

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. የቧንቧ ውሃ ዝርጋታ ዕቃዎች
  2. የቧንቧ መፍቻዎች
  3. ፓምፕ (Pump)
  4. የጽህፈት መሳሪያዎች
  5. የጽዳት ዕቃዎች
  6. የደምብ ልብሶች
  7. የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች
  8. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  9. ሞተር ሣይክል
  10. የሞተር ሣይክል ጎማ እና መለዋወጫ

1. የመኪና ጎማ እና መለዋወጫ ድርጅታችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለምፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ።

1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው

4. የቫትእና ቲን (TIN) ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸዉ።

6 ማንኛውም ተጫራች የሚስገባው ሰነድ በጥንቃቄ ታሽጎ ፋይናንሻል (financial) አንድ (1)ኦርጅናል፣ ቴክኒካል (Technical)አንድ (1) ኦርጅናል፣ (2) ኮፒ ፋይናንሻል financial)ና (2) ኮፒ ቴክኒካል(technical) በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት በሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል። ሰነዱ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።

7. ጨረታው የሚሞላው በነጠላ ዋጋ ነው።

8. በተጫራቾች ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ግልጽና አጠራጣሪ ባልሆነ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ባልሆነ ፅሁፍ ማቅረብ አለባቸዉ።

9. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ማንኛውንም የሃሳብም ሆነ የዋጋ ማሻሻያ በማቅረብ ከጨረታው ውጪ መሆን አይቻልም።

10. የሚቀርቡት ዕቃዎች 1ኛ ደረጃ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ለማሸነፍ ብሎ ዕቃውን የማይመጥን ያልሆነ ዋጋ ሞልቶ ወይም ሰጥቶ እቃዉ ሲቀርብ 2ኛ ደረጃ ከሆነ የማንቀበል መሆኑን አስቀድመን እንገልፃለን።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 600 ብር እያዳንዱ ዝርዝር ላይ በመክፈል ከሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ ድርጅት በሂሳብ እና ፋይናንስ አስተዳደር ስራ ሂደት ክፍል ቀርበው ማግኘት (መግዛት) የሚችሉ መሆኑን።

12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታን ካሸነፈ መስሪያ ቤቱ ናሙና ማቅረብ አለበት ባላቸው እቃዎች ላይ እንደ የውሃ ቧንቧ ዕቃዎች ፣ የቧንቧ መፍቻዎች, የጽዳት ዕቃዎች፤ የደምብ ልብሶች፣ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች ለመ/ቤቱ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።

13. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኃላ በመጀመሪያ የስራ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

14. የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ ውሃ አገልግሎት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ አለበት።

15. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 60,000.00 (ስልሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ እያዳንዱ ዝርዝር ላይ ማስያዝ አለበት። ማንኛውም ተጫራች CPO ሲያቀርብ ለብቻው በፖስታ ማሸግ አለበት። እንዲሁም የሚቀርበው CPO የሚቆይበት ጊዜ 6(ስድስት)) ወር ብቻ መሆን አለበት።

16. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት ጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ እና በስልክ እንደተገለጸ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጋር መፈራረም አለበት።

17. አሸናፊው ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።

18. መስሪያ ቤቱ ከሚደረገው የግዥ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን መገንዘብ አለባቸው።

19. መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

20. በፖስታውና በሰነዱ ላይ ህጋዊ ማህተም፣ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት።

ለበለጠ መረጃ፡- የሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት

ስልክ ቁጥር 022 116 1166/ 022 116 1127

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኃላ በመጀመሪያ የስራ ቀን በ3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-19 10:00
  • Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኃላ በመጀመሪያ የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሞጆ ቆቃ ኤጀርስ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Bid bond: 60,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 600.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T09:41:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders