Spare Parts and Car Decoration Materials

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ. የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/01/2019

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታዉ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አሰፈላጊዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

3. ማንኛዉም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴከኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው

5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም

7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም

8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም

9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡

10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 558 2519/ 0909 273 110

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-19 14:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Geda Transport and Logistics S.C.
  • Buyer address: ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T11:57:36.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders