Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጭርታ ቁጠረ 04/2019

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በሀራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው።

2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም። እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜዉ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ-ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገዉ በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።

3. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለምድብ 4 ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 5 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000(ሃምሳ ሽ ብር)፣ ለምድብ 6 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለምድብ ሀ ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ Cpo በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 28/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ መገኘት አለባቸው።

4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00-12፡00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100፡00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 28/01/2019 ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።

6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት መስከረም 23/2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 28/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ሳያዩ በሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም።

7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

ተቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረተው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ሀራጅ ጨረታ

እስከ 28/01/2019 ከጠዋቱ 3፡3ዐ ድረስ

በ28/01/2019ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።

9.በተጫራቾች የተሰጠ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

10. በጨረታ ለሚሸጥ እቃ የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል።

11. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል። በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው።

12. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።

13. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡።

14. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት። በተጨማሪም ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።

15. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

16. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።

17. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ።

18. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተደደር የስራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559 0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ  ጉምሩክ ቅ/ ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-08 10:00
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T12:41:00.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders