House, Building and Warehouse

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአምቦ ከተማ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ ባለ 7(ሰባት) ወለል ሕንፃ ለንግድ፣ ለቢሮ፣ ለካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአምቦ ከተማ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ ባለ 7(ሰባት) ወለል ሕንፃ ለንግድ፣ ለቢሮ፣ ለካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታውን መመሪያዎች በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን አምቦ ከተማ በሚገኘው አዋሽ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ በማቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለጨረታው መወዳደሪያ የሚሆን የ1 (አንድ) ወር ኪራይ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም በማሰራት በታሸገ ኤንቨሎፕ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አምቦ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አምቦ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።

5. የጨረታው አሸናፊ¬ች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የ3 ወራት የኪራይ ውል መፈፀም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ይጠበቅባቸዋል፣ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ክፍያውን ፈጽመው የኪራይ ውል ካልፈፀሙ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 011-530-31-02/04፣ ወይም
011-236-41-74 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-20 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Awash Bank Share Company
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T13:28:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders