Spare Parts and Car Decoration Materials

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን የተለያዩ እቃዎችን ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር AASA/WSIDD/DOV/NCB/G002/2019

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን፡-

  • ምድብ አንድ፡ የቶዮታ መኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ምድብ ሁለት፡ የፎርድ መኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ምድብ ሶስት፡- የጎማ እና ባትሪ እቃዎች
  • ምድብ አራት፡ የመኪና ጌጣጌጥ እና ልዩ ልዩ እቃዎች
  • ምድብ አምስት፡- ለተሽከርካሪ ጥገና የሚሆኑ የተለያዩ መፍቻዎች(Tools) በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን ዲቪዥን ጽ/ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ በኤሌክትሮኒክስ ማስተላለፍ (አካውንት ቁጥር 1000338000719 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)።
  2. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርትፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኤሌክትሮኒክ ትራንስፈር ለምድብ አንድ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ ሁለት ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ)፣ ለምድብ ሶስት እና አራት ለእያንዳንዳቸው ብር 80,000.00(ሰማንያ ሺህ)፣ ለምድብ አምስት ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርበታል። ይህንኑ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  4. አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈባቸው የዕቃ ዝርዝር የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታ።
  5. የሚገዙ እቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን 20% ሊጨምር ወይም 20% ሊቀንስ ይችላ።
  6. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
  7.  የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  8. ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ 8፡30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  9. ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
  10. ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ሳኒቴሽን

መሰረት ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥ ን

አድራሻ፡ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ8፣ የቦታው ልዩ ስም፡ ልደታ

ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ

ስልክቁጥር፡- +251 11 5579512/9036 (1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)

e-mail- [email protected] 

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-20 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Water and Sewerage Authority
  • Buyer address: ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ-08 ፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T13:55:03.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders