House, Building and Warehouse
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of secure office space) ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ECMNCB/OB/02/2019
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of secure office space) ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንስ እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3.ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ስአት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባቸዋል።
7. አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት።
8. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብየሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
10. አንዱ ተጫራቾ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
11. ጨረታው ጥቅምት 9 ቀን 2019 ከሰዓት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ4:30 ላይ ተጫራቾችና ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
12. በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውንመከፈት አያስተጓጉለውም።
13. ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ረስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ወ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሪስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዬ ህንፃ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡- 011-5-57-83-27
ኢሜል፡- [email protected]
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-19 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
- Posted at: 2026-10-05T14:45:05.000Z
- Source: Qelal Tenders