Materials

የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሕንፃ መሳሪያ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የጭነት እና የህዝብ መኪና ኪራይ አግልግሎት፣ ህትመት እና የካፌ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 001/2019

በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 10 የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ለመደበኛ በጀት የውስጥ ገቢ በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት 3 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 4 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት፣
  • ሎት 6 ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
  • ሎት 7 ቋሚ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣
  • ሎት 8 የሕንፃ መሳሪያ ዕቃዎች፣ እና
  • ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
  • ሎት 10 የጭነት እና የህዝብ መኪና ኪራይ አግልግሎት፣
  • ሎት 11 ህትመት፣ 
  • ሎት 12 የካፌ አገልግሎት።

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እንዲሁም የተጨማሪ  እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተወዳዳሪዎች በግብር ዓመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ ከአምራች ወይም ከአከፋፋዮች የሚሰጥ ውክልና ወይም የእሽሙር ማህበር መመስረቻ ሰነድ እንዲሁም ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶች ተካተው መቅረብ አለበት።
  4. እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ ከአምራች ወይም ከአከፋፋዮች የሚሰጥ ውክልና ወይም የእሽሙር ማህበር መመስረቻ ሰነድ እንዲሁም ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶች ተካተው መቅረብ አለበት።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ በየሎቱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን  መውሰድ ይችላሉ። በተጨማሪም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አያይዘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የዕቃዎች ዝርዝርእናየጨረታማወዳደሪያ ሰነድ ለይ ስማችሁን በመፃፍ ፊርማችሁንና አድራሻችሁን ማስፈርና እንደ ሚታይ አርጋችው ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ስታስገቡ ከሙሉ ፋይል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ጋር እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ 11ኛው ቀን በ 4፡30 በአገሪ ቱሉ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
  9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  10. የማወዳደሪያ ዋጋ ከቫት ጋር መሞላት አለበት።
  11. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበርያ ለሎት 1 ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት 2 ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት 3 ብር 3500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)፣ ለሎት 4 ብር 10,000( አስር ሺህ)፣ ለሎት 5 ብር 1000 (አንድ ሺህ)፣ ለሎት 6 ብር 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)፣ ለሎት 7 ብር 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)፣ ለሎት 8 ብር 5000 (አምስት ሺህ)፣ ለሎት 9 ብር 1000 (አንድ ሺህ)፣ ለሎት 10 ብር 1000 (አንድ ሺህ)፣ ለሎት 11 ብር 2000 (ሁለት ሺህ)፣ ለሎት 12 ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ማስያዝ ይኖርባችዋል።
  12. ት/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት ከውል በፊት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላሉ።
  13. አሸናፊው ድርጀት ዕቃዎቹን እስከ አገሪ ቱሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱትራንስፖርት አጠቃሎ ማስገባት አለበት።
  14. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጃችሁ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት ምርት ወይም እሴት በጨመራችሁት ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ግን እንደ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ መወዳደር የምትችሉ ይሆናል።
  15. ተጫራቾች ዕቃውን እስከ 6 ወር 25% ባስገቡበት ዋጋ መስሪያ ቤቱ ለመጨመር ቢጠይቅ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  16. ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለበት ውድቅ ይሆናል።
  17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 99 111 9100/ 011 230 7230/ 011 230 7301

በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 1ዐ ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ምዕራፍ 2ኛደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ

በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአገሪቱሉ አጠቃላይ 2ኛደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-15 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአገሪቱሉ አጠቃላይ 2ኛደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T10:32:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders