Accounting and Auditing, Accounting System Design
ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር የ2018 ዓ.ም የማህበሩን የሒሳብ ሰነዶች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የኦዲት ሥራ
ጨረታ ማስታወቂያ
ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር ከመስከረም 28/2017 ጀምሮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር 7468 ተመዝግቦ እውቅና የተሰጠው ሀገር በቀል ያለ ትርፍ የሚሰራ ማህበር ሲሆን በሱስ ምክንያት የተጎዱና በጎዳና ላይ የሚኖሩ ወጣቶችን በሕክምናና በሥነ-ልቦና ማገገሚያ ስራዎች ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ በማቋቋም ወደ ተስተካከለና አምራች ሕይወት እንዲመለሱ ለማድረግ የተቋቋመ ድርጅት ነው።
ስለሆነም የ2018 ዓ.ም የማህበሩን የሒሳብ ሰነዶች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፤
ከዚህ በታች በተጠቀሱት መስፈርቶች መሠረት መስፈርቶቹን የሚያሟላ በግልፅ ጨረታ መወዳደር ይቻላል፦
- ተወዳዳሪዎች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች የኦዲት ማድረግ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተወዳዳሪዎች ሥራውን ሠርተው የሚያስረክቡበትን ቀን በጨረታው ማሸነፊያ ሰነድ ላይ መጥቀስ አለባቸው።
ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በአካል በመምጣት እና በስልክ ቁጥር በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ስልክቁጥር ፡- 09 13 58 08 10/ 09 11 86 36 58
አድራሻችን፦ የማህበሩ ጊዜያዊ ቢሮ ሰባራ ባቡር፣ አናንያ ሆስፒታል
ያለበት ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16
ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-07 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ማዕዶት በሱስ የተጎዱ ወጣቶች ማህበር
- Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T10:56:21.000Z
- Source: Qelal Tenders