Spare Parts and Car Decoration Materials

በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ለመምሪያዎች እና ለጽ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የመኪና ጎማ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ለመምሪያዎች እና ለጽ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት

አገልግሎት የሚውል ለኛ ዙር በሎት ጠትላላ ድምር

  • ሎት 1 የመኪና ጎማ
  • ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የታክስ ክሊራንስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለውና ማቅረብ የሚችል

2. የግዥው መጠን ክብር 500,000፡00/ አምስት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቁሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. የሚገዙትን ዕቃ አይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጀቱን ማሕተም ማድረግ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር/200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፍል የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ድሮው ንግድ ባንክ ማግኘት ይቻላሉ።

7. ተጫራቾች በሚሞሉት ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም በተጨማሪም የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መቀመጥ አለበት።

8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጎማ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለመለዋወጫ ዕቃ ብር 80,000 /ሰማንያ ሺህ ብር/ እና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳድር የሥራ ሂደት የቀድሞው ዋናው ንግድ ባንክ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ድረስ በአየር ላይ ይውላል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ማ /ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሠዓት ይከፈታል የጨረታ መክፈቻው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

11. አሸናፊው ድርጅት የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ን/ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ይዞ በመምጣት ማስረከብ አለበት።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 058 771 3362

በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-10-17 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሠዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debre Markos City Administration FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T08:48:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders