Textile, Garments and Uniforms
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 04/02/2019 እና በ07/02/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታአወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን፤ የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቾች ፦
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሸ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
ጫማዎች አልባሳት የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና-አክሰሰሪ- ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፡ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ የቡና ረከቦት እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 እስከ ጠዋቱ 3፡45
|
04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል |
5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
9 ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-17
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-10-17 11:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Afar
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T10:07:15.000Z
- Source: Qelal Tenders