Office Furniture

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለዘመናዊ ጂ+1 ህንጻ አገልግሎት የሚውል ዘመናዊ ኢምፖርት ስታንዳርድ የስብሰባ አዳራሽ ወንበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ግጨ -012/2019

ተቋማችን በአዲስ አበባ ጎፋ በሚገኘው ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት ግቢ ውስጥ ላስገነባው ዘመናዊ ጂ+1 ህንጻ አገልግሎት የሚውል ዘመናዊ ኢምፖርት ስታንዳርድ የስብሰባ አዳራሽ ወንበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

ዘመናዊ ኢምፖርት ስታንዳርድ የስብሰባ አዳራሽ ወንበር ግዥ

65,000.00

ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1.  ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
  2.  ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3.  አድራሻ፡- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት ıኛ ፎቅ ላይ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል ስልክ ቁጥር :- 011-156-01-48
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና < ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY> በሚል መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6.  ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-20 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: 65,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T10:10:12.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders