Textile, Garments and Uniforms
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Amhara
More tags
Cleaning and Janitorial Equipment and ServicePersonal Care Products and ServicesEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesSpare Parts and Car Decoration MaterialsHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingKitchen EquipmentVehicle and Machinery SaleSales, Disposals and ForeclosureVehicle and Machinery ForeclosureOther SalesTelecommunication EquipmentAmharic2merkatoEthiopian Customs Commission
Description
የሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር07-2019
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ
- የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣
- የኮስሞቲከስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
- የመገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
- የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣
- ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ከተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተ/ቁጥር 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም እያስፈልግም።
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።
- ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 05/2019 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር / እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ።
- የግልፅ ጨረታው ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 503 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ሰዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዙ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
- ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል።
- የሐራጅ ጨረታው ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸንፉበትን ዕቃ ዋጋ 5 በአምስት ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖረባቸዋል።
- ከላይ በተቁ 12 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፤ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም።
- ለግልጽ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስመ- ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም።
- በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም
በስልክ ቁጥር 058-320-7418 ወይም 058-320-7569 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሸን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-15
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-10-15 14:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 08, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T14:05:05.000Z
- Source: Qelal Tenders