Equipment and Accessories

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በማረግ ጨረታ እና በሐራጅ  ጨረታ ቁጥር 28/2019፣ 29/2019፣ 30/2019፣ 31/2019፤ 32/2019፣ 33/2019፣ 34/2019፣ 35/2019 እና 36/2019 ለመሸጥ ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ባለመፈጸም ምክንያት እና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ

  • የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • ሞባይሎች፣
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣
  • አልባሳት፣
  • ጫማዎች፣
  • ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ

በግልፅ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 28/2019 በቀን 2/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 29/2019 በቀን 05/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 30/2019 በቀን 09/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 31/2019 በቀን 12/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 32/2019 በቀን 16/02/2019 ዓ ም፣ ጨረታ ቁጥር 33/2019 በቀን 19/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 34/2019 በቀን 23/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 35/2019 በቀን 26/02/2019፣ ጨረታ ቁጥር 36/2019 በቀን 30/02/2019 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በመሆኑም

  1. በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 – 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ(5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን ጥቅምት 02/2019 ዓ/ም፣ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 16/2019 ዓ/ም፣ ጥቅምት 19/2019 ዓ/ም፣ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም፣ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡ዐዐ ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል።
  5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው።
  9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  10. በተራ ቁጥር 01-09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 28/2019 በቀን 2/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 29/2019 በቀን 05/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 30/2019 በቀን 09/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 31/2019 በቀን 12/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 32/2019 በቀን 16/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 33/2019 በቀን 19/02/2010 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 34/2019 በቀን 23/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 35/2019 በቀን 26/02/2019 ጨረታ ቁጥር 36/2019 በቀን 30/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሂድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል።
  11. በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  12. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከሻት በፊት የተሰጠ መሆኑን እናሳውቃለን።
  13. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃልን።
  14. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት፣ ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ስራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ (Online) አሠራር ለማስኬድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ኢማ ጋር ለመሥራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አማ በወረቀት አልባ (Online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።
  16. የኦክሸን ኢትዮጵያ ኢማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251 90 511 5511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 011 668 4537 እና  011 668 4193  ደውለው ይጠይቁ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-09 14:15
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 08, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T14:11:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders