Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር የቂ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት 001/2019 ለ2019 በጀት ዓመት
የተለያዩ
- ሎት 1፡ የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 2፡ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3፡ የደንብ ልብሶች፣
- ሎት 4፡ የተለያዩ ቅርፃቅርጽና የህትመት ውጤቶችን
- ሎት 5፡ ቋሚና አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች
- ሎት 6፡ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች የመኪና ዘይትና ቅባቶች
- ሎት 7፡ የተለያዩ የጥገና እቃዎች
- ሎት 8፡ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 9፡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ የጥገና ስራዎች እና
- ሎት 1ዐ፡- የመስተንግዶ ግዥ ውሀ ሌሎችም ወዘተ…በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ከሚሸጡበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
4. ተጫራቾት የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፣
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በታሽገ ኢንቨሎፕ የእቃው አገልግሎት መጠንና ዋጋ / Financial & Technical envelop በዝርዝር ተሞልቶ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ማስገባት አለባቸው፤
6. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በነጋታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰባተኛ ፎቅ አዳራሽ ይከፈታል፤
7. የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፤
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000009412399 በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ገቢ በማድረግና አድቫይስ ይዞ በመምጣት የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቢሮ የማስገባት ግዴታ አለበት፤
9. አሸናፊው ድርጀት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ቅ/ጽ/ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤
10.ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቄራ ኢትፍሩት ፊት ለፊት መንግድ ተሻግሮ ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ ቅድስት ታወር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የቂርቆስ ክ/ከ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የፋይናንስና ግዥ የሰራ ሂደት
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር 011 4 70 16 63
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-21 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kirkos Sub City Small Tax Payers Bureau
- Buyer address: ቄራ ኢትፍሩት ፊት ለፊት መንገድ ተሻግሮ ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ ቅድስት ታወር ሕንፃ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
- Posted at: 2026-10-09T09:03:06.000Z
- Source: Qelal Tenders