Spare Parts and Car Decoration Materials

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአውቶቡስ ጎማ ጥገና አገልግሎት እና የተሽከርካሪ ባትሪ ጥገና እና እድሳት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አአከአአድ / ብግጨቁ/017/2019

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/017/2019

  • ሎት 1 (የአውቶቡስ ጎማ ጥገና አገልግሎት) እና
  • ሎት 2 (የተሽከርካሪ ባትሪ ጥገና እና እድሳት አገልግሎት) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር ለሎት 1 ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) እና ለሎት 2 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በማቅረብ በግልጽ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ ተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፤
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡ ስልክ ቁጥር: 011 666 3206
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-20 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Organization
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
  • Posted at: 2026-10-09T09:28:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders