Spare Parts and Car Decoration Materials
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የደቡብ ዕዝ ሜንቴናንስ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር ደ/ዕዝ ሜንቴናንስ ግዥ B-01/2019 ዓ/ም
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ቶዮታ ተሸከርካሪዎች የመለዋዎጫ ዕቃ
- የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ኮመርሻል ከባድ ተሽከርካሪዎች የመለዋዎጫ ዕቃ
- የተለያዩ ሞዴል ያላቸው የመኪና ጎማዎች እና ባትሪዎች
- ለጦር መሳሪያና የጦር መሳሪያ ለጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚውል አላቂ የጋራዥ መስሪያ ዕቃዎች
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ከፋይነት/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኤንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 500.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው ደ/ዕዝ ጠ/መምሪያ 1ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ዕዝ ጠ/ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 328 0019 /0988990839/ ይደውሉ
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ
ቶጋ
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-03 10:30
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Ministry of Defense
- Buyer address: መከላከያ ት/ስልጠና ዋ/መ/ግዥ ቡድን ጃል ሜዳ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
- Posted at: 2026-10-09T09:42:15.000Z
- Source: Qelal Tenders