Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 04 ት/ጽ/ቤት የዱዱቢሳ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል

Description

የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 04 ት/ጽ/ቤት የዱዱቢሳ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ እቃዎች ማለትም

  • ሎት1 የትምህርት እቃዎች፤
  • ሎት2 የቢሮ እቃዎች፤
  • ሎት3 የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት4 የደንብ ልብስ፤
  • ሎት 5 ፈርኒቸሮች፣
  • ሎት6 ፕላንት ማሽነሪ
  • ሎት 7 ልዩልዩ መሣሪያዎች፤
  • ሎት 8 የኤለክትሮኒክስ ማሽነሪ ጥገና፣
  •  ሎት 9.የትራንስፖርት እቃ ጭነት ሥራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የደንብ ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።

1.1 በዘመኑ በ2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN NO / ያላቸው።

ተጫራቶች በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ድረገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጀው ክፍል የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2.1 ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በመለየት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለበት።

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ የኢትዮጵያ ብር የክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት።

1.ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት የሚጫረቱበት ዋጋ በሰነድ ላይ በግልፅ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦርጂናል ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከሎት 1 እሰከ ሎት 9 መጫረት ወይም መርጠው አንዱን ወይም ሁለቱን መጫረት ይችላሉ ነገር ግን ከእያንዳንዱ ሎት እቃዎች መራርጠው ለተወሰኑት እቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።

3. የጨረታው ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን በ3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት በይፋ ይከፈታል።

4. ት/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

5. ዱዱቢሳ የመ/ደ/ት/ቤት በግልፅ ጨረታ የተለያዩ የፅዳት ዕቃ፤ የትምህርት እቃዎች፤ የቢሮ እቃዎች፤ ደንብ ልብስ፤ ፕላንት ማሽነሪ፤ ፈርኒቸሮችና ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፤ የኤለክትሮኒክስ ማሽነሪ ጥገና፤ 9. የትራንስፖርት እቃ ጭነት በሠንጠረዥ በቀረበው መሰረት የምትጫረቱበትን ዋጋ ቫትን በመጨመር ሞልታችሁ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. የተጫራቾች መመሪያ

1.2. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት፤ የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፊኬት ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

1.3. ተጫራቾች ከአንድ መቶ ሺህ (100,000.00) ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ዕቃዎች የሚጫረቱ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

1.4. በተ.ቁ 1.2 የተዘረዘሩትን ሠነዶች እያንዳንዳቸው ላይ በአንድ ገጽ ላይ በግልፅ በሚነበብ ሁኔታ ኮፒ በማድረግ በኦሪጂናሉ በማመሳከር ማስገባት አላባቸው።

1.5. የጨረታ ሰነድ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ሲሆን ከሎት 1 እስከ 9 የተዘረዘሩት ዕቃዎች በተዘረዘረው ሠንጠረዥ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በትክክል በመሙላት መፈረም በሚገባቸው ቦታ ላይ በመፈረም በማሕተም ቦታ ማሕተማቸውን በማድረግ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው።

1.6 ት/ቤቱ ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ትተው በሌላ በራሳቸው ሰነድ ዋጋ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ።

1.7 ተጫራቾች ናሙና ያቀርባሉ ተብለው የተዘረዘሩትን እቃዎች ጨረታ ከመዘገጋቱ በፊት በማቅረብ እና በማስመዝገብ ማስረከብ አለባቸው። 

1.8 ናሙናዎቹ ለተሸናፊ ተጫራቶች አሸናፊው እንደተገለጸ ይመለስላቸዋል። ለአሸናፊዎች ተጫራቾች ግን እቃዎችን አስረክበው እስኪያጠናቅቁ ድረስ ለማመሳከሪያነት ቆይተው አስረከቦ

1.9 የጨረታው ሳጥን በት/ቤት የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት በስራ ቀንና ሰዓት ሰነዶችን ማስገባት አለባቸው።

1.10 የት/ቤቱ የጨረታው ኮሚቴ ዕቃዎቹን የሚመርጠው ዝቅተኛ ዋጋ በማየት ብቻ ሳይሆን ጥራቱን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመገንዘብ ናሙና ሲያቀርቡ ጥራቱ የጠበቀ እቃ ማቅረብ አለባቸው።

1.11 በጨረታው ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮችን ማብራሪያ የሚፈልጉ በጽሁፍ ወይም በአካል በስራ ቀንና ሰዓት በት/ቤቱ በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ።

1.12 ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች አይስተናገዱም።

1.12.1 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲ.ፒ.ኦ) ከዚህ በታች በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

 

የሎት ዝርዝር

 

የጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር

የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ብር

ሎት-1

አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

400

30000

ሎት-2

አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

400

40000

ሎት-3

አላቂ የጽዳት ዕቃዎች

400

30000

ሎት-4

የደንብ ልብስ

400

50000

ሎት-5

ፈርኒቸሮች

400

60000

ሎት-6

ፕላንት ማሽነሪ

400

60000

ሎት-7

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

400

50000

ሎት-8

የኤሌክትሮኒከስ ማሸነሪ ጥገና

400

30000

ሎት-9

የትራንስፖርት እቃ ጭነት

400

30000

የኢትዮጵያ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለት/ቤቱ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታው ማስከበሪያ ለአሸናፊ ተጫራቾች ሲፒኦ የሚመለሰው የጨረታ ሂደት ካለቀ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን።

1.13 አሸናፊ ተጫራች ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) የማስያዝ ግዴታ አለበት። 

1.14 ተጫራቾች ላለማጭበርበር እና ሙስና ላለመፈጸም ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘውን ቅጽ መፈረም አለባቸው።

1.15 የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት መሞከር ከጨረታ ወጪ ከማድረጉ በተጨማሪ ለወደፊት በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ያደርጋል።

1.16 አሸናፊው ድርጅት ማሸነፋ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ1ዐ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈረም አለበት። በውል አፈጻጸም ወቅት ከገበያ ዋጋ መቀነሱ ምክንያት ያሸነፈው ድርጅት የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ይችላሉ። ግን ዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይችሉም።

1.17 አሸናፊው ድርጅት የውል መሰረት ግዴታውን ሳይፈፅም ከቀረ ውል ማስከበሪያ ይወረሳል።

1.18 አሸናፊው ድርጅት ለቅድመ ክፍያው ተመጣጣኝ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብ አለበት።

1.19. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀን ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ 7፡30 እስከ 11፡30 መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ ፡- ሲ.ፒ.ኦ የምታሰሩት በዱዱቢሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም መሆኑን እናሳውቃለን። የት/ቤቱ አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ጨርቆስ አደባባይ ለሚ እንጀራ ማዕከል ፊት ለፊት መሆኑን እንገልጻለን።

በአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ
የዱዱቢሳ 1 ኛ ደረጃ ት / ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን በ3፡30
  • Bid opening: 2026-10-22 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dudubisa Primary School
  • Buyer address: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ጨርቆስ አደባባይ ለሚ እንጀራ ማዕከል ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T07:27:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders