Accounting and Auditing, Accounting System Design

አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም አክሲዮን ማኅበር ለ2019፣ 2020 እና 2021 በጀት ዓመት የሚሠራባቸውን የድርጅቱ ሂሳብ ኦዲት የሚያደርግ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

ለኦዲት ሥራ የወጣ ማስታወቂያ

አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም አክሲዮን ማኅበር ለ2019፣ 2020 እና 2021 በጀት ዓመት የሚሠራባቸውን የድርጅቱ ሂሳብ ኦዲት የሚያደርግ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተወዳዳሪ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል።

1. በኦዲት ሥራ ንግድ ፈቃድ ያለው፤

2. የዘመኑ ግብር የከፈለ፤

3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤

4. የ.ተ.እ. ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት፤

5. ከዚህ በፊት ቢያንስ የአምስት ድርጅቶች ሂሳብ ኦዲት ስለማድረጉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

6. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 5000.00 ( አምስት ሺ ) ብር በአክሲዮን ማኅበሩ ስም ሲ.ፒ.ኦ. (CPO) አሠርቶ ማቅረብ አለበት፣

7. የጨረታውን ዶክሜንት የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ) ብር ከፍሎ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 15ኛው የሥራ ቀን 2ኛ ፎቅ ከሚገኘው ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፤

8. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ የሚሠሩበትን ዋጋ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ 6፡00 ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል።

9. አክሲዮን ማኅበሩ ለጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቅቤና ቅመማ ቅመም አክሲዮን ማኅበር

መርካቶ ቃኛው ሻለቃ ሆቴል ጀርባ

ስልክ ቁጥር፡- 09 11 68 49 04 ወይም 09 83 02 73 79

አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም ነጋዴዎች አክሲዮን ማኅበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-28 14:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም ነጋዴዎች አክሲዮን ማኅበር
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T09:12:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders